ወንድ ሁሉ የሴት ራስ ነውን? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በወንድሞችና በእኅቶች የአገልግሎት ሚና ልዩነት ላይ ቢያንስ በሁለት ጎራ የሚመደብ የአተያይ ልዩነት መኖሩ ይታወቃል። ጉዳዩ ዘመን ዘለቅ ሙግት የያዘና ሰፊ በመሆኑ እንደ ዋዛ አልገባበትም። የዛሬ ዓላማዬ አንድ ጥቅስ ብቻ ነው፤ ይኸውም “የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ” የሚለው ነው…
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
频道ይህ የጳውሎስ ፈቃዱ አገልግሎት ሲሆን፣ አብያተ ክርስቲያናትና ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዓላማነት አንግቧል። youtube.com/PaulosFekadu fb.com/PaulsPulpit/
互动与广告
近 30 天帖子聚合
- 平均反应
- 93.9
- 平均评论
- 0
- 平均转发
- 16.8
- 广告帖子(30 天)
- 0
- 广告占比
- 0.0%
- 被提及(30 天)
- 0
榜单位置
各窗口最近一次榜单
暂未进入榜单
频道进入榜单池并满足数据条件后会显示名次。
最近帖子
按发布时间倒序,最多展示 8 条
ኬልቄዶን፣ ቁስጥንጥንያ እና የቤተ ክርስቲያን ፖለቲካ ጉባኤ ኬልቄዶን (451 ዓ.ም.) የቤተ ክርስቲያንን መከፈል ማስከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ የሚያሳዝን ይመስለኛል። በርግጥ ነገረ መለኮታዊ ጉዳይ የጉባኤው ዋና አጀንዳ የነበረ ቢሆንም፣ ነገሮችን ያጦዘውና ያመሰቃቀለው ግን ፖለቲካ ነበር፤ የቤተ ክርስቲያን ፖለቲካ። (እንዳለመታደል ሆኖ ዛሬም ቢሆን፣ በየቱም ስፍራ ያለች ቤተ ክርስቲያን አንዳች የኮመጠጠ ፖለቲካ…
አልሰማነውም እንዳትሉኝ ብቻ! https://youtu.be/6udJjvk-toc?is=cbvDa9Xwdj_uPoKd
https://youtu.be/hC-LwDfxrwE
“ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ልጅ ነበረ” (2ሳሙ. 5፥4)። ዕብራይስጡም “ልጅ” ነው የሚለው። “የ30 ዓመት ልጅ”። ሰምታችኋል! 30ዎች ገና ልጆች ናችሁ። አይዟችሁ! https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0FJrtFFfvY4Szq4GnmrvVevyHx5Ze2VSMS9qvBNXEnmu1r1XvGFkunLNLvgxqBJKwl
የእግዚአብሔር ልጆች ነን። ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ በቅጡ የምንገነዘበው ግን ጌታ ኢየሱስ ሲገለጥ ነው፤ “ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን” (1ዮሐ. 3፥1-2)። የእግዚአብሔር ልጆች ነን። እግዚአብሔር ልጆቹ ያልነበርነውን በክርስቶስ በኩል ልጆቹ አድርጎናል። በመንፈሱ በኩል አዲስ…
“ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች ለይቶ የሚያስቀምጥ አንድ ነገር ምንድን ነው?” ቢባል፣ መልሱ ቀላል ነው፤ ጸጋ። ጸጋ የክርስትና ልዩ ፈርጥ ነው! የኀጢአትና የሰይጣን ባሮችና ምርኮኞች ሰንሰለታቸው ተሰብሮ፣ በነጻነት የሚመላለሱ የእግዚአብሔር ቤተሰቦችና ወዳጆች የሚሆኑበት ምስጢሩ ጸጋ ነው። የኀጢአትና የበደል ክምር ምን ያህል ቢቆለል፣ ወሰን አልባውን የእግዚአብሔር ጸጋ አይሸፍነውም። ጸጋው ኀያል ነውና ከሁሉ የ…
ክናንያ ሲታሰብ በቅድሚያ ከተነገራቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ ("በዘመድ ነው!" ብትሉም ግዴለም😜)። ኳየሩን ለማቋቋም ርምጃዎች ሲጀመሩ አውቃለሁ። ክናንያ ተመሥርቶ አባላቱ ሥልጠና ሲወስዱም እዚያ ነበርሁ፤ አንድ ቀንም አብሬያቸው አሳልፌያለሁ። በዚህ እጅግ እደሰታለሁ። (ይህን ሁሉ የምለው፣ ኅብረቱ በደንብ ታስቦበት ለዘላቂ ጉዞ በዕቅድ መደራጀቱን ለመመስከር ነው።) ባለፉት ዘመናት እንደ ምውት የሆነው የኳየር…
相似频道
基于 Telegram 官方相似频道推荐
暂无相似频道
等待相似频道抓取任务运行。