ጠጠር! . (#ፈይሠል_አሚን) . ከአቅም ሁሉ መሐል. . . እያንጠፋጠፈ፣ካለኝ ከነበረኝ፣ “መጋፈጥ” ብቻ ቀረኝ! እነሆም…. ጎልያዶች ፊት ቆምኩኝ፣አንተን ተማምኜ፤ ታጥቄያለሁ ጠጠር፣ እኔም ዳዊት ኾኜ! . @huluezih @huluezih
ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
频道ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ! . ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤ ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉
互动与广告
近 30 天帖子聚合
- 平均反应
- 48
- 平均评论
- 1.5
- 平均转发
- 9.5
- 广告帖子(30 天)
- 0
- 广告占比
- 0.0%
- 被提及(30 天)
- 0
榜单位置
各窗口最近一次榜单
暂未进入榜单
频道进入榜单池并满足数据条件后会显示名次。
最近帖子
按发布时间倒序,最多展示 8 条
አያነቡንም፣ርእስ ይሠጡናል! . (#ፈይሠል_አሚን) መርምረው አልለዩን፣ ዘልቀውም አላዩን፤ ተቀምጠን በገሃድ፣በጭፍን ያልፉናል፤ አያነቡንም! ርእስ ይሠጡናል! እኔ. . . ለነፍስ የምገለጥ፣ብርሃን የከበበኝ፣ “ሽፋን-አልባ መጽሐፍ ነኝ. . . ልብ ያለው ያንብበኝ! . @huluezih @huluezih
አያልፍልኝም! . (#ፈይሠል_አሚን) . ብጥር አልተሳካም፣ ታግዬ አልቻልኩም፣ በሰው መንገድ ብሔድ፣የእውነት ብብሰለሰል፤ ለእኔ አልተሠጠም፣ ይኼን ጊዜ መምሰል! አይሳካም ለእኔ፣ ከቶ አያልፍልኝም፣ መቼም ከፍ አልልም፣አሁን ካለሁበት፤ መምሰል፣ጭራ መቁላት. . . ስለማልችልበት! . @huluezih @huluezih
. . .of the day!😎
ዐውቀዋለሁ ልቤን… “ቀረሁበት እንጂ፣የቀረብኝ የለም”፣ ብዬ ሳልታበይ… ለጊዜ ሠጠሁት፣ ፍርዱን አክለፍልፎ፣ቀኑን በቀን ያምጣ፤ እናያለን ያኔ. . . ማን ማንን እንዳጣ! . (#ፈይሠል_አሚን) . @huluezih @huluezih
መስከረምን እወዳታለሁ! (8) #ፈይሠል_አሚን (በዓመት አንድ ቀን ብቻ የሚነበበው ተከታታይ ታሪክ እነሆ ስምንተኛ ዓመቱ wow!😮) . ይህን ስናገር ዛሬ ሰዎች እንደሚገምቱት ልቤ አይደነግጥም። እንደቀድሞም አይሰበርም። አሁን ልቤ ብዙ ነገር አይገርመውም። መስከረምን ያክል እኩል እሣት፣እኩል በረዶ የገጠመው በምን ይገረማል? የሰው ልጅ በየዓመቱ አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ሕይወት እጀምራለሁ ይላል። እኔ ግን የጀመ…
ብዙ ነው ያየሁት! . (#ፈይሠል_አሚን) . ከጊዜ ቀድሜ… በዚህች አጭር ዕድሜ. . . ብዙ ዐየሁ የማይታይ! ብዙ አጣሁ የሚታይ አፍርሶ እየሠራኝ፣ነቅሎ እየገጠመኝ፣ ምድር ከዘራችው፣የለም ያልገጠመኝ! ብዙ ነው ያየሁት. . . ሩቅ ነው የመጣሁት. . . ብቻ በመንገዴ “ደንታ” ነው ያጣሁት! . @huluezih @huluezih
የት ነው? . (#ፈይሠል_አሚን) . አምላክ የት ነው ያለው? ምድር ላይ ወይስ በሰማይ ቤት? ብለው ሲጠይቁኝ.... መልስ አለ እኔ ዘንድ በፅኑ የማምነው ጊዜና ሥፍራ ድቅድቅና ብራ ምንም ሳይቀይረው ምንም ሳይወስነው "አምላክ ከኔ ጋር ነው!" . @huluezih @huluezih
相似频道
基于 Telegram 官方相似频道推荐
暂无相似频道
等待相似频道抓取任务运行。