መዝሙር 51 ልዩ መዝሙር ነው። ዳዊት ይህንን መዝሙር ለመቀኘት ቢዘገይም—በኦርዮ ላይ ያደረሰው በደል ዓመት ቢያልፈውም—ለዘመንና ለሁሉ የሚሆን ሐሳብ ተቀኘ፤ በመካከልም እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም” (ቍ. 17)። እግዚአብሔር ያጣው የተሰበረ መንፈስ (ተስፋ የቆረጠ አይደለም) እንጂ ስለ ኅጢአት የሚቀር…
Daily Injera
频道A Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible everyday in partnership with @ethbiblica. www.dailyinjera.org Follow us on FB • IG • Twitter • Viber • YT - @dailyinjera
互动与广告
近 30 天帖子聚合
- 平均反应
- 22.2
- 平均评论
- 0
- 平均转发
- 3.9
- 广告帖子(30 天)
- 30
- 广告占比
- 100.0%
- 被提及(30 天)
- 0
榜单位置
各窗口最近一次榜单
暂未进入榜单
频道进入榜单池并满足数据条件后会显示名次。
最近帖子
按发布时间倒序,最多展示 8 条
የመጀመሪያው መሥዋዕት አቀራረብ ሁለት ዐይነት ነበር፤ መሥዋዕቱ ቢለያዩም፣ ዋና ልዩነት የሆነው ግን አቀራረቡ ነው። ቃየን እንደ ገበሬነቱ ከምድሪቱ ፍሬ 'እንደ ነገሩ' አቀረበ፤ “አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎቹ መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ” (ዘፍ 4፥4)። ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን ሳይመለከት ቀረ። እርሱ ከእጃንም (ከምንሰጠው) ሆነ ከን…
ጥበብ ሁለት ገጽታ እንዳላት ያዕቆብ ገለጠ። አንዲቷ ከታች፣ ሌላኛዪቷ ደግሞ ከላይ። ሁለቱም በምንጫቸውና በፍሬያቸው ይለያሉ--ክፉና መልካም። “ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ ዕሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት" (ያዕ 3፥17 )። ላኛዪቱ ምንጯን ትወክላለች፤ የሰላሙን ጌታ። እውነተኛም ስለሆነች ዕረፍት አትነሳም። ይል…
#ArtSaturdays "ሕይወትን" የሚፈልጉ "መልካም ቀኖችን" ሊያዩ የሚወድዱም ምን መሆንና ማድረግ እንዳለባቸው የዕብራውያን ጸሐፊ ዘረዘረ፤ "ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም" (1ጴጥ 3፥11)። ሰላምን የሚፈልጉና የሚከተሏት፣ ከክፋት እየራቁ ይሄዳሉ፤ ልክ ከአንድ ሰፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የሚሄዱ ሰዎች መነሻቸውን እንደሚርቁት። መልካም ድርግጊት ደግሞ ሰላምን መከተያ አንዱና ዋናው…
የጳውሎስ መልእክቶች ሁሉ (13ቱ) አጀማመራቸው ተመሳሳይ ነው። ለግለሰቦች የተጻፉት መጋቤ መልእክታት ጭምር፤ “ለተወዳጁ ልጄ፣ ለጢሞቴዎስ፤ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ከእግዚአብሔር አብ፣ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ይሁን” (2ጢሞ 1፥2)። ሰላም በምሕረትና በጸጋ ትታጀባለች። እግዚአብሔር ከሰዎች ጋራ ሰላም ያደረገው ምሕረት አድርጎ ነው። ጸጋም ሰላምን ለማቆየት አቅም ነው። ከመለኮት (አብና ወልድ፣ በመንፈስ ቅዱ…
የሰላም ምርቃት ትልቅ ነው። ከጌታ የሆነ ሰላም ሲሆን ደግሞ፣ እጅግ ታላቅ ይሆናል፤ “የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም ነገር ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን” (2ተሰ 3፥16)። ክርስቶስ ጌታ "የሰላም ልዑል" ነው፤ ሰላምን ሲሰጥ ከራሱ እንጂ ከሁኔታ ወይም ከውጫዊው ነገር (ቀድቶ) አይደለም። ሰላሙ ሁኔታን ያልፋል፤ ያሳልፋልም። እንዲሁም፣ ኀልውናውን ትከተላለች፤ "ጌታ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን" እንደ ተ…
ሮሜ 12፥9-21 የጳውሎስን ግሩም ትእዛዝ ይዟል። የፍቅርን ሰፊ አውታር የዳሰሰው ይህ ክፍል፣ ሰላም ጥረት ፈላጊ ስለ መሆኗ ገልጿል፤ "ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ" (ቍ. 18)። ሰላም ከክስተት ብቻ አይደለም፤ አቅም ነው። ከጌታ የተቀበልነው ሰላም ፍጹም ቢሆንም፣ ሰዎች ስለሆንን እርስ በርስ የምንጋራው ሊደፈርስ ይችላል። ስለዚህ፣ ትኩረትና ጥረት ይፈልጋል—"ቢቻላችሁስ"—እንደ ተባለ። እ…
"ከሰላም ልዑል" (አለቃ) በላይ የሰላምን መገኛና ባሕርይ የሚያውቅ የለም። እርሱም እንዲህ አለ፤ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም” (ዮሐ 14፥27)። ሁኔታዎች ሊለወጡ፣ ሰላምም ሊደፈርስ ይችላል፤ ጌታ የሚሰጠው ሰላም ግን መቀመጫው በምድር--በሁኔታዎች-- ሳይሆን በሰማይ ስለሆነ፣ የትኛውም የረብሻ ትነት አያገኘውም። እር…
相似频道
基于 Telegram 官方相似频道推荐
暂无相似频道
等待相似频道抓取任务运行。